
ይህ መጽሀፍ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ 1983 አም መጀመሪያ እስከ 1988 አም መጨረሻ በጅማ ጤና ሳይንስ ኢንስቲቲዩት (ጅጤሳ) የህክምና ትምህርት ቤት እያለሁ በእለት ማስታወሻዬ የከተብኳቸውን፤ በኋላም ከግንቦት 2012 አም እስከ ነሐሴ 2014 አም በፌስቡክ ገጼ ላይ አኑሪያቸው የነበሩትን በርካታ የግል ማስተወሻዎችና ወጎች አንድ ላይ በመጠረዝ የተዘጋጀ መጽሀፍ ነው። ማስታወሻዎቹ በህክምና ትምህርትቤት ውስጥ በመማር ሂደት የነበሩ የስሜት ውጣ ውረዶችና ሌሎችም ሁኔታዎች በአመዛኙ ፈገግታን በሚያጭር መልኩ የተዘገቡበት ነው። በ 1983 አም ኢትዮጵያን ያስተዳድር የነበረው የደርግ መንግስት ከትግራይ አማጺያን (ህወሀት) ጋር ያካሂድ ለነበረው ጦርነት መላው የኢትዮጵያ ኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በውትድርና እንዲሰለጥኑ በተወሰነው መስረት ወደ ብላቴ ማሰልጠኛ ጣቢያ ከተጋዙት በርካታ ተማሪዎች ውስጥ አንዱ ስለነበርኩ የብላቴ ዘመቻ ታሪኬና አስገራሚ አጋጣሚዎቼም በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ተካተዋል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የቀረበው ጽሑፍ ከዋናው ማስታወሻ መያዣ (አጀንዳ) ላይ ሙሉ በሙሉ የተገለበጠ ሳይሆን መሠረተ ሐሳቡ ሳይዛነፍ፣ ስነ ጽሑፋዊ ውበት እንዲኖረው የአርትኦት ሥራ ተሰርቶለት የተዘጋጀ ነው። ከዋናው ማስታወሻ ላይ ከተውጣጡት በተጨማሪ አሁን ላይ ሆኜ በምልሰት የጻፍኳቸውም ተካተዋል። እነዚህ ግን በመጠን በጣም አናሳ ናቸው። ጽሑፉ ፈገግታን ከማጫር በተጨማሪ አንባቢን ባለፉ ጊዜያትና ድርጊቶች ላይ አንተርሶ ወደ ግል ትዝታ ሊያስገስግስ ይችላል። አንባቢው ሀኪም ከሆነ ደግሞ ወደኋላ ሄዶ የራሱ የህክምና ትምህርት ቤት አጋጣሚዎች እንዲቃኝ ይረዳው ይሆናል። የዚህ ዘመን የህክምና ተማሪዎች፣ በተለይም የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ተማሪዎች ምናልባት ይህንን ጽሑፍ የማንበብ እድል ከገጠማቸው ከሰላሳ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ስለነበረው የህክምና ትምህርት አሰጣጥ መጠነኛ ግንዛቤ ሊሰጣቸው ይችላል። ማስታወሻው ባጠቃላይ በኢትዮጵያ በ1980ዎቹ የነበረውን የህክምና ተማሪዎች ህይወት እንዲሁም የኢትዮጵያን ሁኔታ በከፊል ስለሚያሳይ ታሪካዊ ፋይዳም አለው።
መልካም ንባብ።
ዶ/ር ሳምሶን ኃይሌ ኃንቃ
Details
- Publication Date
- Jun 24, 2023
- Language
- Amharic
- ISBN
- 9781312416529
- Category
- Biographies & Memoirs
- Copyright
- All Rights Reserved - Standard Copyright License
- Contributors
- By (author): Dr. Samson Hanka
Specifications
- Pages
- 200
- Binding Type
- Paperback Perfect Bound
- Interior Color
- Black & White
- Dimensions
- A5 (5.83 x 8.27 in / 148 x 210 mm)