ልማት

ልማት

ንድፈ ሃሳብ እና ትግበራ

ByYohannes Aberra Ayele

This ebook may not meet accessibility standards and may not be fully compatible with assistive technologies.
ለራስ የሚበጅ ትክክለኛው የልማት ንድፈ-ሀሳብና የሌሎች የተግባር ልምድ ምርጫ ላይ በዓለም ዙሪያ ክርክሮች በስፋት እየተካሄዱ ነው። ምርጫው ትክክለኛ የሚሆነው ምርጫውን ከየማህበረሰቦቹ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ አውድ ጋር ለማዛመድ ሲቻል ነው፡፡ እንዲሁም የልማት ጽንሰ-ሃሳቦችን፤ ንድፈ-ሃሳቦችንና መርሆዎችን በስፋት በማወቅና መልካም ልምዶችን በጥልቀት በመገምገም ነው፡፡ በማደግ ላይ ባለው ዓለም ያለው አጠቃላይ አዝማሚያ የልማት ጎዳና ምርጫዎች በውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት የሚመሩ መሆናቸው ነው። በአንደኛው ወይም በሌላኛው አገር የተሳኩ የልማት ንድፈ-ሃሳቦች፤ መርሆዎችና ልምዶች በታዳጊ ሀገራት ኢኮኖሚ ውስጥ ጥቅም አለን በሚሉ የውጭ መንግስታት፤ ተቋማት፤ ቡድኖችና ግለሰቦች በመድሃኒት ማዘዣ መልክ ይላካሉ፡፡ የተለያዩ ታዳጊ ሃገራት የልማት አሳዛኝ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት በጭፍን ነገር ግን በጋለ ስሜት የተቀበሉትን ተግባራዊ ባደረጉ በርካታ ሃገራት ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ችግር እየደረሰ ነው፡፡ ምን ያህል ተገቢ ምርጫ እንደሆነ ሳይመረምሩና የአካባቢያቸው ሁኔታ በቅጡ ሳይረዱ ተግባራዊ ያደረጉት የልማት አቅጣጫ ውጤቱ አስከፊ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ መጽሓፍ በልማት ረገድ ሁለቴ አስቦ አንዴ በውጤታማነት ለመዝለል፤ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ወደ ዘላቂ ልማት የሚያመራውን ጎዳና ለመምረጥ የሚያስችል መጠነኛ አስተዋጽዖ ሊኖረው ይችላል። ልማትን በዘላቂነት ጎዳና የሚያራምድ እውቀት የፖለቲካ መሪዎችና የኤክስፐርቶች ሞኖፖል ሆኖ ሊቀር አይገባም፡፡ የልማት እውቀት በሰፊው ህዝብ እጅ ካልገባ የህዝብ የተሟላ የልማት ተሳትፎ እውን ሊሆን አይችልም፤ ያለ ህዝብ የነቃ ተሳትፎ ልማት የጨለማ ጉዞ ነውና፡፡ መጽሃፉ የሚከተለው ይዘት አለው፦ የልማት ጽንሰ-ሃሳቦች፤ እሴቶች፤ ገጽታዎችና ዘላቂነት፟፡፡ የልማት ንድፈ-ሃሳቦችና ፓራዲሞች:: መተዳደሪያ: ድህነት፣ አለመመጣጠን:: የልማት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ:: የለውጥ ንድፈ-ሃሳብ፤ ክትትልና ግምገማ፡፡ ልማት፦ የዘርፍ ፣ ዘርፍ-ተሻጋሪና ጂኦግራፊያዊ:: የልማት አለም ዓቀፍ ትግበራዎች/ልምዶች:: ግጭትና የድህረ-ግጭት መልሶ-ግንባታ፡፡ የልማት ዘርፍ የስኬት ልኬቶች መድብል፡፡ ዋቢ ጽሁፎችና ተጨማሪ ንባቦች፡፡

Details

Publication Date
Jan 31, 2025
Language
Amharic
Category
Business & Economics
Copyright
All Rights Reserved - Standard Copyright License
Contributors
By (author): Yohannes Aberra Ayele

Specifications

Format
PDF

Keywords

Ratings & Reviews